Saturday, 25 Apr 2015
You are here: Home

Main Menu

Downloads

Calender

«  April 2015  »
MTWTFSS
 12345
6789101112
13141516171819
20212223242526
27282930 
Welcome to Website of Debre Berhan Univeristy
Latest Events in DBU

በዩኒቨርሲቲው የባህል ማዕከል የግዕዝ ቋንቋ ተናጋሪዎች ቤተሰብ ተመሰረተ

በደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ባህል ማዕከል የግዕዝ ቋንቋ ተናጋሪዎች ቤተሰብ መጋቢት 24 ቀን 2007 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡ የቋንቋው ተናጋሪዎች ቤተሰብ መመስረቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳለው የምስረታ ስነ ስርዓቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

የምስረታ ስነስርዓቱን በንግግር የከፈቱት የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ የጥናትና ምርምርና ህብረተሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ተፈሪ አድነው በአገራችን በግእዝ ቋንቋ የተፃፉና አለም አቀፋዊ ጠቀሜታ ያላቸው ጥንታዊ መዛግብት በብዛት እንደሚገኙ ገልፀው ቋንቋው የነባር እውቀትና መረጃ ምንጭ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

የቀድሞው ባህልና ታሪካችን የተፃፈበት የግእዝ ቋንቋ በአለም አቀፍ ደረጃ የበርካታ ጥናትና ምርምሮች ማዕከል ሆኖ ይገኛል ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ዳግም አንሰራርቶ የሚጠበቀውን አገራዊ ጠቀሜታ እንዲያስገኝ ዩንቨርሲቲው የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ ተናግረዋል፡፡ 

የዩንቨርሲቲው የባህል ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ዝናወርቅ አሰፋ በግዕዝ ቋንቋ ምንነትና አመጣጥ ዙሪያ ባቀረቡት የመወያያ ፅሑፍ በተለይም በአገሪቱ የመካከለኛው ዘመን ታሪክ ቋንቋው በስነ ፅሑፍ ረገድ ወደ ከፍተኛ ደረጃ የተሸጋገረበት እንደነበር ጠቅሰው በተለያዩ ምክንያቶች በቤተ ክህነት አካባቢ ብቻ ሊወሰን መቻሉን አስረድተዋል፡፡

በበርካታ የአገሪቱ አካባቢዎች በተፈጥሯዊም ሆነ ማህበራዊ ዘርፎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ጥንታዊ የብራና መፃህፍት በግዕዝ ቋንቋ ተፅፈው እንደሚገኙ በመወያያ ፅሁፋቸው ያመለከቱት አቶ ዝና መዛግብቱን ጥቅም ላይ ለማዋል በተለይም ቋንቋው ስርዓተ ትምህርት ተቀርፆለት በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች እንዲሰጥ በማድረግ በኩል መንግስት የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የዩንቨርሲቲው የድህረ ምረቃ ትምህርት ቤትና የታሪክ መምህር የሆኑት ዶክተር ደረሰ አየናቸው በበኩላቸው በጀርመኑ ሃምቡርግ እና በጣሊያኑ ፓሪስ ዩንቨርሲቲዎች በትምህርት ክፍሎች ደረጃ እየተሰጠ ከመሆኑም ባሻገር ሰፊ ጥናትና ምርምር እየተካሄደበት አስረድተው በአገራችንም ተመሳሳይ ተግባራትን ለማከናወን በዩኒቨርሲቲው ውሥጥ የተመሰረተው የቋንቋው ተናጋሪዎች ቤተሰብ ጅምር እንቅስቃሴ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡


ኢንስቲቲውቱ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚጋዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ

ስልጠና ሰጠ

የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ትምህርት ኢንስቲቲውት ጃፓይጎ ከተሰኘ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያግዝ የግንዛቤ ማስጨባጫ ስልጠና ሰጠ፡፡ 

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ የጥናትና ምርምርና ህብረተሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ተፈሪ አድነው እንዳሉት ስልጠናው በተለይም የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ረገድ በህክምና እና ጤና ሳይንስ ትምህርት ኢንስቲቲውት በመካሄድ ላይ ያለውን ጅምር እንቅስቃሴ ወደ ሌሎች ኮሌጆች ለማስፋት ያስችላል፡፡

የትምህርትን ጥራት የማስጠበቅ ተግባር ለስነ ትምህርት ኢንስቲቲውት ብቻ የሚተው ሃላፊነት አለመሆኑን ያስገነዘቡት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የተዛቡ አመለካከቶችን በመቅረፍና ሁሉም የዩንቨርሲቲው አካላት ለትምህርት ጥራት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ በማስቻል ረገድ ስልጠናው የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡

የዩንቨርሲቲው የትምህርት ጥራትና አግባብነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶክተር ደረጀ አንዳርጌ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት ጥራትን የማስጠበቅ ተግባር ተመራቂ ተማሪዎች በኢንዱስትሪዎች እና በሌሎች ቀጣሪ ድርጅቶች ከሚኖራቸው ተፈላጊነት ጋር የተያያዘ በመሆኑ ትልቅ ትኩረትን የሚሻ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም ተከታታይነት ያለው የምዘና የክትትልና የግምገማ ስራ በሁሉም የትምህርት ክፍሎች ሊከናውን እንደሚገባው የጠቀሱት ዳይሬክተሩ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ትምህርት ኢንስቲቲውት በስሩ የመሰረተው የልማት ማዕከል ተግባራቱን በተሻለ መልክ ለመፈፀም እንዳስቻለው ገልፀዋል፡፡

የህክምና እና ጤና ሳይንስ ትምህርት የልማት ማዕከል አስተባባሪ የሆኑት መምህር ተስፋ ደጀኔ በበኩላቸው የልማት ማዕከሉ ከተመሰረተ ወዲህ የተግባር ልምምድ ቦታዎች መረጣና ምዘና፣ የተማሪዎችና የፈተና ምዘና፣ የስልጠና፣ የክህሎት ማበልፀጊያ ቤተ ሙከራዎች መከታታያ ቅፅ ዝግጅት እና የስርዓተ ትምህርት ግምገማ ተግባራት ማከናወኑን ገልፀዋል፡፡

ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል በኮምፒውቲንግ ኮሌጅ መምህር የሆኑት አቶ የሻለም ገዛኸኝ በተለይም በምህንድስና እና ሳይንስ ዘርፎች የኢንዱስትሪውን ፍላጎት የሚያረኩ ተማሪዎች አፍርቶ ለማበርከት ዩንቨርሲቲው በቂ የስራ ላይ ልምምድ እና ትምህርታዊ ጉብኝቶችን ማመቻቸት ይኖርበታል ሲሉ ሃሳባቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

Read more...