VACANCY ANNOUNCEMENT

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትን አወዳድሮ ለመቅጠር የወጣ ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና ዩኒቨርሲቲውን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ፍላጎቱና ብቃቱ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድሮ የላቀ ውጤት ያመጣውን/ችውን ተወዳዳሪ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አድርጎ ለመመደብ ይፈልጋል፡፡

1. ስለ ዩኒቨርሲቲው አጭር መግለጫ

ዩኒቨርሲቲው ከአዲስ አበባ የ 2 ሰዓት የመኪና ጉዞ ሐኸኀኀኸርቀት ላይ በምትገኘው ጥንታዊና ታሪካዊ በሆነችው የደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኝ ሲሆን በ1999 ዓ.ም ከተመሰረቱ 10 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በትምህርት ሚኒሰቴር መስፈርት መሰረት ከፍተኛ ደረጃ ያለው ተቋም ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ከ 2ሺህ በላይ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በመያዝ ከ 30ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ የሚገኝ እና በሚሰራቸው የመማር ማስተማር፣ የምርምርና የማህበራዊ አገልግሎት ሥራዎች በኢትዮጵያ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡

2. የሥራው መደብ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

3. የማመልከቻ መስፈርቶች

3.1 የትምህርት ደረጃ፡- ሶስተኛ ድግሪ (PhD) ወይም ሁለተኛ ድግሪ (MA/MSc) እና ቢያንስ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያለው/ያላት፣

3.2 የሥራ ልምድ፡- በከፍተኛ ትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በከፍተኛ አመራር/ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ች፣

3.3 ስትራተጂያዊ እቅድ ማቅረብ፡- አመልካቾች በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ከፍተኛ የጥናትና ምርምር እና የማሕበረሰብ አገልግሎት ለማሳካት ስለሚከተሉት ስልት፤  ዩኒቨርሲቲውን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ስለሚሰጡት አመራር፤ ሀገራዊና ዓለማቀፋዊ አጋርነትንና ትስስርን ለማሳደግ ስለሚከተሉት ዘዴ፣ የሠራተኞችን ተነሳሽነትና ቆራጥነት ለማሳደግ ስለሚያከናዉኗቸው ተግበራት ወዘተ የሚገልጽ ከ10 ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ እቅድ በፅሁፍ ያቀርባሉ፤ የጽሑፉ መጠን፡- ፎንት፡ ቪዥዋል ግዕዝ፤ የፎንት መጠን 12፤ በመስመሮች መካከል ያለው ርቀት 2 (double space) መሆን አለበት፡፡ ስላቀረቡት እቅድ ለዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ስታፍና ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች በሚዘጋጀው መድረክ ላይ ገለፃ ያደርጋሉ፡፡

3.4 እድሜ፡- አመልካቾች እድሜያቸው ከ60 ዓመት ያልበለጠ መሆን አለበት፡፡

3.5 ፆታ፡- ማስታወቂያው ወንዶችንና ሴቶችን የሚያጠቃልል ሲሆን፣ መስፈርቱን የሚያሟሉ ሁሉ እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፡፡

4. ተፈላጊ ክህሎቶች

4.1 የአመራር ክህሎት፡- አመልካቾች በዩኒቨርሲቲው ያለውን የሰው፣ የገንዘብና የቁሳቁስ ሃብት በማስተባበር፣ ለመምራት የሚያስችል ዕቅድ በማቀድ፣ የአሠራር፣ የክትትል፣ የድጋፍና ቁጥጥር ሥርዓትን በመዘርጋት፣ ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን በማስፈን የአካዳሚክና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችን የሥራ ተነሻሽነትና የባለቤትነት ስሜት ለማሳደግና የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮና ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል የአመራር ክህሎት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

4.2 አዲስ አሰራር የመፍጠርና ለውጥ የማምጣት ክህሎት፡- አመልካቾች በዩኒቨርሲቲው ለውጥና እድገትን ለማምጣት የሚያስችሉ አዳዲስ የአሰራር ስልቶችን የማመንጨትና ተግባራዊ የማድረግ አቅም ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

4.3 የተግባቦት ክህሎት፡-አመልካቾች በዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ካሉ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አገራዊ፣ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የዩኒቨርሲቲውን ተልዕኮና ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል የተግባቦት ክህሎት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

5. ተፈላጊ ሥነ-ምግባራዊ ባህርያት

5.1 አመልካቾች ከሥነ-ምግባር ጉድለቶች የፀዱ፣ በመልካም ባህርያቸውና በስራ አክባሪነታቸውና ታታሪነታቸው የተመሰከረላቸውና ለሌሎች አርአያነታቸው የጎላ መሆን አለባቸው፡፡

5.2 አመልካቾች ተግባብቶ የመስራት፣ ሁሉን በእኩል የማስተናገድ፣ ለሚቀርቡላቸው ጉዳዮች ተገቢውን ምላሽ በተገቢው ጊዜ የመስጠት መርህ የሚከተሉ መሆን አለባቸው፡፡

6. የምደባ ሁኔታ

በውድድሩ የላቀ ውጤት በማምጣት የተመረጠው/ችው አመልካች ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲን ለ 6 አመታት በፕሬዚዳንትነት የሚመራ/የምትመራ ሲሆን የፕሬዚዳንትነቱ ጊዜ እንዳስፈላጊነቱ ሊራዘም ይችላል፡፡

7. ደመወዝና ጥቅማጥቅም

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ስኬል መሰረት፤

8. የማመልከቻ ጊዜ

ተወዳዳሪዎች ማመልከቻቸውን ፣ CV እና ኦርጅናል የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃቸውን እንዲሁም ከ 10 ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ እቅድ (ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር) ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመስከረም 23/2012 ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እና  ሠዓት በአካል ማቅረብ፤ ወይም በኢሜይል መላክ፣ ወይም በፖስታ መላክ ይኖርባቸዋል፡፡

9. የማመልከቻ ቦታና ማቅረቢያ መንገዶች

9.1 በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ምልመላና መረጣ ኮሚቴ ጽ/ቤት በግንባር ማቅረብ ወይም

9.2 ለዚሁ ሥራ ብቻ በተዘጋጀ ኢ-ሜይል አድራሻ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. .et መላክ ወይም

9.3 በፖስታ፡ 445 መላክ ይችላሉ፡፡

10. ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት መንገዶች መጠየቅ ይቻላል

10.1 በቢሮ ስልክ ቁጥር፡ +251118697134 ወይም በሞባይል ቁጥር፡ +251913066022

10.2 በኢ-ሜይል አድራሻ: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. .et

10.3 በዩኒቨርሲቲው ዌብ ሳይት: www.dbu.edu.et

 

የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አመራር ቦርድ

 

 

 

VACANCY ANNOUNCEMENT

[For the Position of the President of Debre Berhan University]

Debre Berhan University (DBU) invites all interested individuals who can meet the requirements to apply for the post of the President of Debre Berhan University.

1. SUMMARY OF INSTITUTION

Debre Berhan University is located in Debre Berhan city, one of the ancient and historical cities of Ethiopia, which is only at a 2-hour driving distance from Addis Ababa. DBU was established in 2007, and is the leading University among the 10 second generation universities established in accordance with the standards of the Ministry of Education of the Federal Government of Ethiopia. It has more than 2,000 teaching and support staff, and has currently enrolled more than 30,000 students. DBU aspires to be one of the preferred universities in Ethiopia in the higher academic learning-teaching, research and community services.  

2. JOB TITLE

President of Debre Berhan University

3. APPLICATION REQUIREMENTS

3.1 Educational Qualification: PhD degree or MA/MSc degree with a rank of Assistant Professor or above.

3.2 Experience: higher level leadership experience in higher education institutions or the industry or research institutes or any institutions having similar missions.

3.3 Presentation of Strategic Plan: The applicant is required to submit his/her strategic plan not more than 10 pages describing his/her leadership direction that he/she would be following on: ensuring quality education, establishing high level research and community service systems, realizing the university center of excellence, partnership and networking approach with national and international partners, elevating human resource motivation and dedication strategies etc. prepared with Times New Roman, font size 12 and double space between lines. This includes a presentation of his/her plan to an audience comprising the academic/support staff and student representatives of the University.

3.4 Age: Applicants over 60 years old are NOT eligible.

3.5 Gender: Both males and females who meet the requirements are encouraged to apply.

4. REQUIRED SKILLS

4.1 Managerial Skill: The applicant is required to possess managerial skill that enables him/her to fulfill the University’s mission and vision by organizing the human, financial and material resources of the University.

4.2 Innovative Skill: The applicant is required to possess the potential to generate novel working strategies and tactics that would promote change and development in the University.

4.3 Interactive Skill: The applicant is required to possess interactive skill that would enable him to advance learning-teaching, research and community services in a bid to strengthen the University’s overall capacity and make it a center of excellence by establishing partnerships and collaboration with national, continental and global institutions.

5. ETHICAL QUALITIES

5.1 The applicant is required to be free from any form of ethical defect and should be one with a confirmed record of exemplary qualities of respect for and commitment to duty.

5.2 The applicant is required to possess the ability of working with others and treating all equally and fairly.

6. TERMS OF ASSIGNMENT

The selected individual serves as President of the Debre Berhan University for a period of 6 years that might be extended if necessary.

7. SALARY AND BENEFITS

Salary will be as per the Debre Berhan University scale.

8. DURATION OF APPLICATION

Applicants can submit applications together with their CV and original testimonials with non-returnable copies, including a copy of his/her strategic plan within 15 working days and time after the announcement on the Ethiopian Herald Magazine.

9. HOW AND WHERE TO APPLY

9.1 Personally at the Office of the search and selection committee, Debre Berhan University or

9.2 By e-mailing to: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  or

9.3 Through p.o.box  at: 445

 

10. FOR MORE INFORMATION

10.1 Telephone No፡ +251118697134 OR Mobile No፡ +251913066022

10.2 E-mail address: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

10.3 Debre Berhan University Website: www.dbu.edu.et

 

THE GOVERNING BOARD OF DEBRE BERHAN UNIVERSITY

 

 

CONTACT US

Communications Affairs Directorate 

Tel: +251116816286

Fax- 0116812065

Po.Box: 445

FPR@dbu.edu.et

Nigus Tadese (PhD)

DBU President

JoomShaper