Monday, 26 Jan 2015
You are here: Home

Main Menu

Downloads

Calender

«  January 2015  »
MTWTFSS
 1234
567891011
12131415161718
19202122232425
262728293031 
Welcome to Website of Debre Berhan Univeristy
Latest Events in DBU

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ሰጠ

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2006 ዓ.ም በስምንት ኮሌጆች ከሚገኙ 33 የትምህርት ክፍሎች ከ1ኛ-3ኛ ዓመት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 63 ሴት ተማሪዎችና 21 ወንድ ተማሪዎች ሽልማት ሰጠ፡፡

በዕለቱ ዶ/ር ታምሬ ዘውዴ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዩኒቨርሲቲው በተለይ ለሴት ተማሪዎች የተለያዩ የማበረታቻ ድጋፎች በየዓመቱ እንደሰጠ ገልፀው በ2006 ዓ.ም በየኮሌጁ ከሚገኙ የትምህርት ክፍሎች ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የሚሰጥ ሽልማት ከማበረታቻዎቹ አንዱ አካል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ በዚህ ዓመት ይህን ሽልማት ለየት የሚያደርገው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተዘጋጀው የሴት ተማሪዎች አቅም ግንባታ ስልጠና ወቅት መሆኑን ገልፀው፤ ለተሸላሚ ተማሪዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ክብርት ፎዚያ አማን የኢፌዲሪ እምባ ጠባቂ ተቋም በሚኒስትር ማዕረግ ዋና እምባ ጠባቂ በሽልማት ስነ ስርዓቱ ተሸላሚ ተማሪዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ለስልጠናው ትኩረት በመስጠት በመከታተልና አሉ ያሏቸውን ችግሮች በግልጽ በማውጣት በንቃት በመሳተፋቸው ስልጠናው እንዲሳካ ላደረጉት የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና አሰልጣኞች ምስጋና አቅርበው የተግባር ሰው እንሁን በማለት መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ 1ኛ ለወጡ ተማሪዎች ሽልማት ሰጥተዋል፡፡

በተጨማሪም 2ኛ እና 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች ሽልማት የሰጡት የተከበሩ  ወ/ሮ እምዩ ቢተው እና ወ/ሮ በላይነሽ  ኩምሳ የሰሜን ሸዋ ዞን ሴቶች ህፃንትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡

በሽልማቱ ስነ-ስርዓት 1ኛ ለወጡ 1000 ብር 2ኛ ለወጡ 700 ብር 3ኛ ለወጡ 400 ብር ዩኒቨርሲቲው ለማበረታቻ በሽልማት መስጠቱ ተገልጾ፤ ሌሎች ተማሪዎችም በትምህርታቸው ጠንክረው እንዲሰሩ በማሳሰብ የፕሮግራሙ ፍፃሜ ሆኗል፡፡


ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለሴት ተማሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከኢፌዲሪ እምባ ጠባቂ ተቋምና ከተወካዮች ም/ቤት አባላት ጋር በመተባበር ለሴት ተማሪዎች ከታህሳስ 4-5/4/2007 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናውን የከፈቱት ዶ/ር ታምሬ ዘውዴ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዚዳት ሲሆኑ፤ የስልጠናውን አስፈላኒነትና ዓላማ ገልፀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በመቀጠልም የሴቶች ታሳታፊነት፣ ተጠቃሚነትና ውጤታማነትን ለማረጋገጥ የሴት መምህራንን ድርሻ ለማጉላት፣ የተማሪዎችን አቅም ለመገንባትና የራስ ተነሳሽነትን ለመፍጠር እንዲሁም በችግሮች ላይ በመመካከር በዘላቂነቱ ዙሪያ ላይ ውሳኔ ለማስተላለፍ ስልጠናው ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል፡፡

ስልጠናው የኢትዮጵያ ሴቶች ትግል ታሪክና ውጤት በክብርት ወ/ሮ ፎዝያ አማን በኢፌዲሪ እምባ ጠባቂ ተቋም በሚኒስትር ማዕረግ ዋና እምባ ጠባቂና በተከበሩ በወ/ሮ እምዩ ቢተው፣ ወ/ሮ ዘውዲቱ ቆንጆ፣ ገነት አባት፣ ወ/ሮ ካሣነሽ አዲስ እና በላይነሽ ኩምሣ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተዘጋጀ የውይይት ሀሳብና የህይወት ክህሎት ስልጠና በዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራን የቀረበ ሲሆን ሰልጣኝ ተማሪዋችም ከስልጠናው ጽንስ ሀሳብ በመነሳት በቡድን ውይይታቸው በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የተለያዩ ጥያቄዎችና በሴት ተማሪዎች ላይ የሚፈፀሙ በደሎችንና ችግሮችን በማንሳት ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ ስልጠናውም አቅም እንደፈጠርላቸው ገልፀው የዚህ ዓይነቱ መድረክ ቀጣይነት እንዲኖረው ሀሳብ አቅርበዋል፡


የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአካል ጉዳተኞች ቀን ተከበረ

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት የአካል ጉዳተኛነት ቀንን “አካል ጉዳተኞችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ” በሚል መሪ ቃል ህዳር 26/2007 ዓ.ም አከበረ፡፡

በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር ሰይድ መሐመድ የውጭና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ፤ የአካል ጉዳተኛነት መንስኤዎችና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታን መፍጠር የዜግነት ግዴታ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ዳይሬክተሩ በዩኒቨርሲቲያችን የአካል ጉዳተኞችን መብቶች በማክበርና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ በማድረግ ልማትን ማረጋገጥ እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡

መ/ር ታረቀኝ የአካል ጉዳተኝነትን በዓል ምክንያት በማድረግ የበዓሉን ዓላማ፣ የአካል ጉዳተኝነት መንስኤ፣ ትርጉም፣ ፓሊሲዎች እንዲሁም አካል ጉዳተኞች የሚገጥሟቸውን ችግሮችና የሚደረግላቸው ድጋፍ፤ በተጨማሪም ከትምህርት ተቋማት ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ሁኔታዎችን በሚመለከት ለውይይት መነሻ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ በመነሻ ሃሳቡ በመነሳት የበዓሉ ተሳታፊዎች በንቃት ሰፊ ውይይት በማድረግ በዓሉ ተፈጽሟል፡፡

Read more...