የአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ

October 09, 2026

የአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ

በ2019 ዓ/ም ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች እና በ2018 ዓ/ም በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሪሜዲያል /ማካካሻ ትምህርት ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም የአንደኛ አመት የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 11 እና 12/2019 ዓ.ም ስለሆነ በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳወቅን፤ ከጥቅምት 13-15/2019 ዓ/ም ልዩ ስልጠናና ኦሬንቴሽን የሚሰጥበት፣ ጥቅምት 16/2019 ዓ/ም ትምህርት የሚጀምርበት ጊዜ መሆኑን እንገልጻለን፡፡