About

የፕላንና መረጃ ዳይሬክቶሬት

 1.1.  የክፍሉ ሚና

የተቋሙን የዕድገት አቅጣጫ የሚያመላክት አሳታፊ የረጅም እና አጭር ጊዜ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ ሥራ ላይ መዋሉን መከታተልና መገምገም፤

የአፈፃፀም ሪፖርቶችን ከሚመለከታቸው ዘርፎች በማሰባሰብ አጠናቅሮ በካውንስል፤ በማኔጅመንት ኮሚቴ እና በቦርድ በማስገምገም ለት/ሚ/ር እና በተወካዮች ምክር ቤት ለሠው ሀብት ቋሚ ኮሚቴ ማስተላለፍ፤

የዩኒቨርሲቲውን የተለያዩ መረጃዎችን አሰባስቦ በማጠናቀር እና በማደራጀት ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ማቅረብና መረጃውን ተደራሽ ማድረግ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ፕሮግራም በጀት ጥያቄ ማዘጋጀት እና የተመደበው የመደበኛ፤ የካፒታል እና የውስጥ ገቢ በአግባቡ ለታሰበው ሥራ መዋሉን መከታተል ነው፡፡

1.2. የክፍሉ ራዕይ

በ2012 በዕቅድ የሚመራና በዘመናዊ መረጃ የተደራጀ ዳይሬክቶሬት መሆን::

1.3. የክፍሉ እሴቶች

 • ዕቅድ ለውጤት
 • የተደራጀ መረጃ
 • ጥራት ያለው አገልግሎት
 • ተነሳሽነት
 • በተናጠል /በቡድን መስራት
 • ውጤታማነት
 • ምቹ ከባቢ ለሠራተኞች

 1.3. በዳይሬክቶሬቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች

 1.3.1. ዕቅድንበተመለከተ፡-

 • የተቋሙን መሪ ዕቅድ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ወር ላይ አዘጋጅቶ ለክፍሎች መላክ፣
 • ሁሉምየሥራሂደቶች /ክፍሎች ዕቅዱን አዘጋጅተው በላኩልን 1 ወር ውስጥ የተቋሙን ዋና ዕቅድ በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው አካላት መላክ፣
 • ሁሉም የሥራሂደቶች/ ክፍሎች የተከለሰ ዕቅድ አዘጋጅተው ባመጡልን በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ የማጠቃለል ሥራውን በማጠናቀር ለሚመለከታቸው ተደራሽ ማድረግ፣

1.3.2.  ሪፖርትን በተመለከተ፡-

 • የሩብ ዓመቱ እንደተጠናቀቀና የቀጣዩ ሩብ አመት በጀመረ የመጀመሪያ ቀን ከሥራ ሂደቶች የተላከውን የሩብ አመት፣ እስከ ሩብ አመቱ ማጠቃለያ ያለውንና አመታዊ የተጠቃለለ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖረት ከዩኒቨርስቲው ዕቅድ አንፃር በማየት ማጠናቀር፣
 • የ6 ወራትና የአመቱን ሪፖርት እንደተጠናቀቀ በ2ኛው ቀን የተጠናቀረውን የዩኒቨርስቲውን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውንስል ከተገመገመና፣ማሻሻያ ከተደረገ በኋላ በቦርድ እንዲገመገም ተደርጎ ማስተካከያ ማድረግ፣
 • በየደረጃው ተገምግሞ የደረሰንን ማስተካከያ ሀሳብ በመውሰድ እንደገና በማስተካከል ለትምህርት ሚኒስቴርና ለተወካዬች ምክር ቤት ሩብ አመቱ ተጠናቆ የቀጣዩ ሩብ አመት መጀመሪያ ወር በ9ኛው ቀን ማስተላለፍ፣
 • የሩብ አመቱ እና የተጠቃለለ የዩኒቨርስቲው የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ተገምግሞ ለሚመለከታቸው አካላት በተላከ  በ15 ቀን ውስጥ ግብረ መልስ ለሥራ ክፍሎች መላክ ፡፡
 • የበጀት ባለሙያ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ጋር በመሆን መረጃዎችን በተከታታይ በማሰባሰብ የቀጣይ አመቱን እና የ 3 ዓመቱን ፕሮግራም በጀት ጥያቄን መጋቢት ወር ላይ ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ማስተላለፍ፣ 

1.3.3.  መረጃን በተመለከተ፡-

 • በዳይሬክቶሬቱ ተጠናቅረው የሚገኙትን መረጀዎች በተጠየቁ  በ15 ደቂቃ ውስጥ እንሰጣለን፣
 • በእጃችን የሌሉ መረጃዎችን ከሌሎች በማሰባሰብ ለጠያቂ አካል መስጠት
 • ማንኛውንም የዕቅድ ፣ሪፖርትና መረጃ ሙያዊ ድጋፍ ለክፍሎቹ መስጠት፡፡
 • የተሰበሰቡ መረጃዎችን ማጠናከርና ትንተና ማድረግ / በግራፍ በሠንጠረዥ በየፋይላቸው ማጠናቀርና ለተጠቃሚ ማሠራጨት፡፡
JoomShaper