Press Release

 ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ያከናወናቸውተ ግባራት ላይ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ


በዓለማችን ብሎም በሀገራችን ከፍተኛ የስብአዊ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቦናዊ ቀውስ እያደረሰ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እንዲቻል ደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከዞን አስተባባሪ ኮሚቴው ጋር በመሆን ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛለ፡፡ በዚሁ መሰረት፡-
1. የመከላከልና የህክምና ሥራዎች ፣
1.1. ቫይረሱን የመከላከል ሥራን በተመለከተ፣ ዩኒቨርሲቲው በዞንና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር የዩኒቨርሲቲው የጤና እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎችን በማቀናጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ በሞንታርቦ ቅስቀሳ፣ በራሪ ወረቀቶች በማሰራጨት፣ በሲዲ የተቀረፁ መልዕክቶችን በማዘጋጀት ለቀበሌዎች፣ ለወረዳዎች እና ለዞን የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤቶች አባዝቶ በመስጠት፣ ፖስተር፣ ባነር እና LED Screen በማዘጋጀት የግንዛቤ ፈጠራ ሥራውን አስፍቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ በርካታ ስልጠናዎችን ለጤና ባለሙያዎች፣ ለምግብ አዘጋጆችና የተዘጋጁ የQuarantine እና Isolation ክፍሎች ለሚያጸዱ ሰዎች ተሰጥተቷል፡፡
1.2. Case management ሥራዎችን በተመለከተ ከዞኑ ጋር በመቀናጀት የዩኒቨርሲቲው የህክምናና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን እና ሜዲካል ዶክተሮች በቅንጅት በመስራት በዞኑ ውስጥ ያሉ ሁሉም አካባቢዎች ላይ ምልክቱን የሚያሳዩ ግለሰቦች ካሉ የመለየት እንዲሁም የreferral system በመስራት ከተጠርጣሪዎች ናሙና ተወስዶ እንዲመረመሩ የማድረግ ሂደቱን በአግባቡ በመስራት የሙያ ግዴታቸውን እየተወጡ ይገኛሉ ፡፡ እስከአሁን ድረስ 8 ተጠርጣሪዎች ናሙናቸው ወደ አዲስ አበባ ተልኮ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል ፡፡
1.3. የለይቶ ማቆያ እና የህክም መስጫ ቦታ ዝግጅትን በተመለከተ፣ የ07 ቀበሌ ጠባሴ ጤና ጣቢያ ፣ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ደግሞ 13 ብሎኮችን ጨምሮ ለQuarantine እና Isolation በተሟላ መልኩ በቁሳቁስ በማደራጀት ዝግጁ ያደርገ ሲሆን ማንኛውም ተጠርጣሪ ከተገኘ ለይቶ ለማቆየትና ወደ ሚመለከተው ምርመራና ህክምና ለመወሰድ የሚያችል ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል ፡፡
2. የገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍን በተመለከተ
2.1. ደ/ብርሃን ከተማ ላይ የሚገኘውን የሀበሻ አረጋዊያን ማእከልን በተመለከተ ከዚህ በፊት ከህብረተሰቡ ድጋፍ የሚያገኙ ከ100 በላይ አረጋዊያ ያሉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲው ሙሉ በሙሉ እነዚህን አረጋዊያን ተረክቦ ቁርስ ፣ ምሳ እና እራት እየመገበ ሲሆን ከምግብ በተጨማሪ የንጽህና መጠበቂያ ሳሙና እና ሳኒታይዘር በመደገፍ ላይ ይገኛል ፡፡
2.2. በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉ የኬሚስትሪ ፣ የጤና ፣ የኬሚካል ኢንጅነሪግ እና የባይሎጂ መምህራን በአንድ ላይ በመሆን በኬሚስትሪ ቤተ ሙከራ ውስጥ 3000 ሊትር በላይ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘር በማዘጋጀት እንዲሁም ከ1000 ሊትር በላይ የተገዛ የንጽህና መጠበቂያ በድምሩ 4000 ሊትር በላይ የእጅ ንጽህና መጠበቂያዎችን በማዘጋጀት በዞኑ ውስጥ ላሉ ሆስፒታሎች ፣ ጤና ጣቢያዎች ፣ ለዞን እና ለወረዳ መስሪያ ቤቶች፣ ለሀበሻ አረጋዊያን ማዕከል እና ለመሳሰሉት ተቋማት በማሰራጨት ላይ የሚገኝ ሲሆን ለጤና ጣቢያዎቹ ለሆስፒታሎች እና ለአረጋዊያ ማዕከሉ ከእጅ ንጽህና መጠበቂያ በተጨማሪ በአንኮበር ምርምር የተገኘውን የመጸዳጃ ቤት ንጽህና መጠበቂያ 500 ሊትር ፈሳሽ ሳሙና እንዲደርሳቸው እየተደረገ ነው ፡፡
2.3. የቀበሌ 07 ጤና ጣቢያን እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን 13 ብሎኮች ለQuarantine እና Isolation ለማዘጋጀት ከ600,000 ብር በላይ በገንዘብና በቁሳቁስ እንዲሁም በዞን ደረጃ ለተቋቋመው አብይ ኮሚቴ ሥራ ማስኬጃና ልዩ ልዩ ሥራዎች የሚውል 500,000 ብር በድምሩ 1,100,000 ብር በጥሬ ገንዘብና በቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ከምንም በላይ የዩኒቨርሲቲው የጤና ባለሙያዎች ፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና አመራሮች እየሰሩት ያለው ሥራ እጅግ በጣም አመርቂና በእንዲህ አይነት የችግር ወቅት በርግጥም በጋር በመስራት ችግሩን መመከት እንደሚቻል ጥሩ ማሳያ የሚሆን ነው፡፡
3. ምርምርና ሳይንሳዊ ድጋፍ ከማድረግ አንፃር
በሀገር ደረጃ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች በየቤታቸው እንዲቆዩ እየተደረገ ቢሆንም የደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የጤና ባለሙያዎች ፣ አንኮበር ላይ ምርምር የሚያደርጉ መምህራን እና የኮምፒውቲንግ ኮሌጅ ፣የሜካኒካልና የኤሌክትሪካል ትምህርት ክፍሎች መምህራን የሚከተሉትን ሀገራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ሥራዎች በቢሮና በላብራቶሪ ውስጥ በመመራመር ላይ ይገኛሉ ፡፡
3.1. ሀገራዊ የኮሮና ቫይረስ Surveillance Data Base ማዘጋጀትን በተመለከተ፡ የጤና እና የኮምፒውቲንግ ኮሌጅ መምህራን በጋራ በመሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚያስችል የመረጃ ቋት በሀገር ደረጃ መኖር ስላለበት Map Based የሆነ የመረጃ ቋት እየተዘጋጀ ሲሆን ይህን የመረጃ ቋት ዝግጅት ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከማህበረሰብ ጤና አገልግሎት ኢንስቲትዮት ፣ ከኢኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዲሁም ከመረጃ ደህንነት ተቋማት ጋር ለማቀናጅትና ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ነው ፡፡ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
3.2. የአፍ ፣ የአይንና የጆሮ ማፅጃ ሳኒታይዘር ዝግጅትን በተመለከተ እስከ አሁን ድረስ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር በየተቋማቱ እየተዘጋጀና አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን ለአፍ ፣ ለጆሮ ፣ ለአፍንጫ እና ለአይን ማጽጃ የሚሆን ሳኒታይዘር ግን እየተዘጋጀ አይደለም በመሆኑም የአንኮበር የመድሃኒት ምርምር ላይ እየተሳተፉ ያሉ የኬሚስቲሪ ፣ የኬሚካል ኢንጅነሪግ እንዲሁም የጤና ሳይንስና ክክምና ኮሌጅ የሜዲሲን መምህራን በጋራ በመሆን ምርምር በማድረግ ለአፍ ፣ ለአፍንጫ ፣ ለአይንና ለጆሮ ማጽጃ የሚሆን ሳኒታይዘር ለማዘጋጀት ልዩ ጥናት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በተለይ የአፍ ማጽጃዉ / የንጽህና መጠበቂያዉ/ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደ ስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
3.3. በተመሳሳይ መልኩ የመካኒካልና የኤሌክተሪካል ትምህርት ክፍሎችና የህክምና ኮሌጅ መምህራን በአንድ ቡድን ተደራጅተው በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ህመም ላይ ለሚገኙ ታማሚዎች የመተንፈሻ ችግራቸውን ለማቃለል እንዲቻል ሜካኒካል ቬንትሌተር በወርክሾፕ ውስጥ እየሰሩ ሲሆን ፕሮቶታይፕ/ናሙናው በቅርብ ቀን ተጠናቆ አስፈላጊውን ሂደት ካለፈ በኋላ ወደ ሙሉ ምርት የሚገባ ይሆናል፡፡
በአጠቃላይ ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ህብረተሰቡን ለማገልገል ከፍተኛ ዝግጅት አድርጓል፡፡

 


መጋቢት 29/2012 ዓ.ም
ዶ/ር ንጉስ ታደሰ
የደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

 

JoomShaper