Event News

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ በ02/10/2011 ዓ.ም ከተማሪዎች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል በውይይት መድረኩም የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተዋል። በጥቅሉ በመድረኩ የተነሱት ሃሣቦች:-

1. ዶርም በመቃጠሉ ቁጣቸውን ገልፀዋል ያቃጠሉ አካላትንም አውግዘዋል።
2. በአማራና ኦሮሞ መካከል ጠብ የለም ከዚህም በኋላ ግጭት ለመፍጠር የሚሰሩትንም እናጋልጣለን።
3. የተለያዩ ጥያቄዋችን እና የመፍትሄ ሀሳቦችንም ሰንዝረዋል። ለተነሱት ጥያቄዋችም የህግ የበላይነትን ባከበረ እና ባለው አሰራር መሰረት መታየት እንዳለበት ተግልጿል።
4. በጥቅሉ ውይይቱ ዩኒቨርስቲው ወደ መደበኛ ሁኔታው ለመመለስ መደላድል የፈጠረ ሆኖ ተገኝቷል።

ዩኒቨርሲቲው


 

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ጊዚያት አንዳንድ አለመረጋገቶችን ለመፍጠር በተለያዩ አካላት ሲሞከር ቆይቷል፡፡ በዚህ መሰረት በተነሱ የተማሪዎች አለመግባባት የመማር ማስተማሩ ሂደት ከ27/9/2011 ዓ.ም ጀምሮ ተስተጓጉሏል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታትም የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት የተለያዩ ጥረቶችን ዕያደረገ ይገኛል፡፡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋርም ሰፊ ውይይት በማድረግና በማረጋገት የሰው ህይዎት እንዳይጠፋና አስከፊ ጉዳት እንዳይደርስ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሠራ ይገኛል፡፡ በተለያየ ጊዜ በዩኒቨርሲቲው ጥፋት ለማድረስና መማር ማስተማሩን ለማወክ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ 58 ተማሪዎች ላይም የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ርምጃ ወስዷል፡፡ አለመረጋጋቱን ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱትም ውስን ተማሪዎች ሲሆኑ ከዩኒቨርሲቲው የተባረሩና ዝቅታኛ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች በማስተባበርና በመምራት በስፋት ይገኙበታል፡፡
ተማሪዎችን ለማረጋገት፣ ደህንነታቸውን ለመጠበቅና መማር ማስተማሩን ወደነበረበት ለመመለስም ዩኒቨርሲቲው በየደረጃው ካሉ የዞን፣ የክልልና የፌደራል መስሪያ-ቤቶችና ሀላፊዎች እንዲሁም ከክልሉና ከፌደራል የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለማስተካከል እየሰራና እያወያየ ባለበት ወቅትም በቀን 1/09/2011 ከምሽቱ 2፡30 አካባቢ በ 2(ሁለት) የተማሪዎች መኖሪያ ህንፃዎች ላይ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል፡፡ቃጠሎውም የህንፃዎቹን ኮርኒስ በማያያዝ የተጀመረ ሲሆን ከከተማ አስተዳደሩና ከሀበሻ ቢራ ጋር በመሆን የጊቢውና የአካባቢው ማህበረሰብ ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ተችሏል፡፡ በአደጋው በሰው ሂዎት ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጉዳት የሌለ ሲሆን አደጋውን በማድረስ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ እየሰራ ይገኛል፡፡ 
በመሆኑም የተማሪ ወላጆች ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና የፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ልጆቻችሁን በመምከርና ከጥፋት እንዲታቀቡ በማድረግ እንድታረጋጉና እንዲሁም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ዕየተራገቡ ያሉ አሉባልታዎች በንፁሀን ተማሪዎች ህይዎት ቁማር መጫወት ሲሆን ተራ የግለሰብና የቡድን አጀንዳን የምታራምዱና ድርጊቱን ለማባባስ የምትሞክሩም ከድርጊታቸሁ እንድትቆጠቡ እናሳስባለን፡፡

ዩኒቨርሲቲው

JoomShaper