በተማሪዎች ዙሪያ የሚሰሩ አካላት ተገቢውን ድጋፍና እገዛ ሊያደርጉ ይገባል ተባለ

News

 ስልጠናው በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ርህራሄ የተሞላ ምላሽ ለተማሪዎች መስጠት በሚል የተዘጋጀ ሲሆን ከተማሪዎች ጋር የሚደረጉ መልካም ግንኙነቶች በተማሪዎች ውጤት ላይ የሚኖራቸው አውንታዊ ምላሽ ከፍተኛ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡ 

በዲኬቲ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ፕሮጀክት አስተባባሪና የባዮ ሜዲካል ሳይንስና የስነልቦና ባለሙያ አቶ ሽመልስ ገበየሁ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች በርካታ ፈተናዎች ያጋጥሟቸዋል ብለው እነዚህን ፈተናዎች ተቋቁመው ለማለፍ የሚደርጉት ትግል ብቻውን በቂ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ባለሙያው አክለውም ጤናማ፣ ውጤታማና አምራች ዜጋ ለማፍራት በተማሪዎች ዙሪያ የሚገኙ አካላት ሁሉ ተገቢውን ድጋፍና እገዛ ሊያደርጉላቸው ይገባል ሲሉም ነው የገለጹት፡፡