College of Education overview
Vision
The College of Education (COE) at the University of Debre Berhan, envisions a state and nation where every individual has equal access to life-long learning and opportunities for healthy development and where each person’s distinct abilities are cultivated from potential to achievement. We bring to this vision a dedicated and highly-regarded faculty, staff, and student, committed to equity and social justice, who encirclement diversity and community as central to the process and outcomes of education, and who seek and bring research-based innovation to our most intractable educational problems.
College Priorities
Equity and Diversity
We will become a renowned institution which improves the educational opportunities and outcomes in classrooms filled with diverse learners by preparing and supporting educational and human development researchers, practitioners and leaders committed to goals of equity and achievement for all.
Innovation and Creativity
The COE will become an influential institution for using the learning sciences to understand how people learn in the 21st century.
Research
We will create research-based knowledge that will guide and enable all stakeholders to work, prosper, and make informed decisions as the boundaries of knowledge continue to expand.
Partnerships
Through partnerships, the College of Education will be a catalyst for learning, research, and action.
Resource Allocation and Administrative Efficiency
To fulfill the university’s vision, the College will commit to the highest standards for efficient and effective use of its resources. Maximize operational efficiency at all activities.
Academic Expansion
The COE is committed to providing the highest quality graduate and professional education at Doctoral and Master’s levels. College of Education will offer Master and doctoral degrees, programs which provide in advance both programs place COE will be the finest in Ethiopia.
Goal
To support the University’s vision to transform while enhancing the college’s build nationwide, the COE will intensify its efforts to offer its own majors and students across campus an outstanding and rigorous educational experience. There will be:-
- Continuous improvement of teacher education programs, so that graduates can develop and implement equitable, relevant learning opportunities for students, including those with special needs, in diverse classrooms;
- Access to high quality learning experiences for majors outside the formal classroom;
- Opportunities for students in other majors to engage in issues related to teaching, learning, and human development, especially with regard to equity and diversity as part of their general education; and
- Research opportunities in which students can explore current challenges and issues in teaching, learning, and human development.
- Service to the community through regular reports detailing how high achieving high school graduates succeed at public higher education institutions.
መማር ማስተማር
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ1999 ዓ.ም የመማር ማስተማሩን ስራ የጀመረው በEducation Faculty በ7 Department እንደመሆኑ መጠን በመደበኛው መርሀ-ግብር 955 ምሩቃንን በዘርፉ አፍርቷል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በክረምቱ መርሀ-ግብር ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ዳይሬክተሮችና ሱፐርቫይዘሮችን በመቀበል በትምህርት አመራርና አስተዳደር (Educational Planning and Management/EdPM) የመጀመሪያ ዲግሪ ለመስጠት በ2ዐዐ3 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን፡-
- EdPM………..…498 ተማሪዎች
- PGDT……..……335 ተማሪዎች በአግባቡ እያስተናገደ የሚገኝ ኮሌጅ ነው፡፡
በ2ዐዐ8 ዓ.ም 5ዐዐ የሚሆኑ የPGDT ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
HDP ስልጠና
የስነ-ትምህርት ኮሌጅ በዩኒቨርሲቲው ዕቅድ በመመራት የትምህርት ጥራት ለማምጣትና ለማስጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትጋት በማገዝ ላይ ይገኛል፡፡ ይኸውም በኮሌጁ ስር ያሉትን የስነ-ትምህርት ባለሙያዎች በማስተባበር በቀጥታ በመማር ማስተማሩ ተግባር ከመሰማራት በተጨማሪ በልዩ ልዩ የአቅም ግንባታ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በሌሎችም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠውን የትምህርት ጥራት ለማምጣትና ለማስጠበቅ የሚቻለው የመምህራኑን የማስተማር ብቃት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ የስነ-ትምህርት ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተ ጀምሮ በየዓመቱ በርካታ መምህራንን HDP በማሰልጠን አስመርቆ ወደ ስራ አሰማርቷል፡፡ HDP በአጠቃላይ መልኩ የመምህራንን የማስተማር ጥበብ ዘመናችን በሚፈቅደው ዓይነት በተግባራዊ ልምምድ ጭምር የሚሰለጥኑበት በመሆኑ ለከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህራን እንደሙያ ፈቃድ የሚወሰድ ሆኗል፡፡
ከ2ዐዐዐ ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2ዐዐ5 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲው መምህራን በተጨማሪ ከደ/ብርሃን መምህራን ኮሌጅ እና ከደ/ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 438 መምህራን ለምረቃ ያበቃ ሲሆን በያዝነው 2ዐዐ7 የትምህርት ዘመንም 40 መምህራን ለመመረቅ የሚያመቃቸውን ስልጠናና ተግባር እያከናወኑ ናቸው፡፡
በዩኒቨርሲቲው ከምንሰጠው የHDP ስልጠና በተጨማሪ ትምህርት ሚኒስቴር በሰጠን ኃላፊነት መሰረት በደብረ ብርሃን መምህራን ኮሌጅ የሚሰጠውን የHDP ስልጠና ካሁን ቀደም እንዳደረግነው ሁሉ የModeration /ክትትል/ ስራ በወር 1 ጊዜ በማድረግ ስልጠናው ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን እያረጋገጥን እንገኛለን፡፡
ስነ-ትምህርት ኮሌጅ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን ትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ የመምህራን አቅም በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ከሚገነባባቸው አይቀሬ የስልጠና መስኮች አንዱ ልዩ ልዩ ስነ-ትምህራታዊ /Education/ ስልጠና ሲሆን በዚህ ስልጠና Student Centered Teaching and
Learning Approach, Active Learning, Continuous Assessment, Measurement and Evaluation እና Modular Approach of Teaching and Learning System ተካተውበት በዩኒቨርሲቲው አዲስ ለተቀጠሩ፣ ከትምህርት ለተመለሱና በዝውውር ለተመደቡ መምህራን ሲሰጥ ቆይቷል እየሰጠም ይገኛል፡፡
ማህበረሰብ አገልግሎት
የስነ-ትምህርት ኮሌጅ በዩኒቨርሲቲው በሚሰጠው የማህበረሰብ አገልግሎት መስክ ትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ልዩ ልዩ ስልጠናዎች በመስጠት ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ እሙን ነው በዚህም መሰረት፡-
- ከማህበረሰብ አገልግሎት እና ከማህበራዊ ሳይንስ እና ሂዩማኒቲስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በ9 ዓይነት የስልጠና ዘርፎች ማለትም /በተግባራዊ ጥናትና ምርምር፣ በመሰረታዊ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች አዘገጃጀት፣ የልዩ ፍላጐት ተማሪዎች ክትትልና ድጋፍ፣ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎቶች፣ በፈተና አዘገጃጀት፣ በተከታታይ ምዘና፣ እለታዊና ዓመታዊ የትምህርት ዕቅድ አዘገጃጀት፣ በኘሮጀክት አዘገጃጀት እና የምክር አገልግሎት አሰጣጥ እና ስነ-ዘዴ ለተለያዩ ጉድኝት ማዕከላት፣ ለመደበኛ ት/ቤቶችና ሳተላይት ት/ቤቶች ስልጠናዎቹን በተጠናከረ መልኩ እየሰጠ ይገኛል፡፡
ጥናትና ምርምር
ስነ-ትምህርት ኮሌጅ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን ትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ችግር ፈቺ የሆነ ጥናትና ምርምር አካሂዷል፡፡
ሀገራዊ ፋይዳ ያለው ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ማካሄድ በ2ዐዐ7 ዓ.ም ከተቀመጡ ቁልፍ የውጤት መስኮች አንዱና ዋነኛው ሲሆን የስነ-ትምህርት ኮሌጅም ይህንን የዓመቱን ቁልፍ የውጤት መስክ ለማሳካት ባስቀመጠው ዕቅድ መሰረት 3 የተጀመሩ ጥናቶች እያካሄደ ይገኛል፡፡
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከል /ELIC/
በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ውስጥ የማስተማሪያ ቋንቋው እንግሊዘኛ እንደመሆኑ መጠን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከል /ELIC/ የተለያዩ የእንግሊዘኛ ማሻሻያ ኘሮግራሞችን በማዘጋጀት የመምህራንን ብሎም የተማሪዎችን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ክህሎት ለማዳበር በእጅጉ እየተነቀሳቀሰ ያለ ማዕከል ሲሆን በእዚህኛውም ዓመት የተለያዩ የክርክር መድረኮችን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች በማዘጋጀት፣ የፊልም ምሽቶችን በማዘጋጀት እና እንዲሁም ለት/ቤቶች የተለያዩ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማሻሻያ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ የሚገኙ ማዕከል ነው፡፡