መስከረም 19/2018 ዓ.ም (ትሎሚ)፡- የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ከአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታ እና ከደብረ ብርሃን ዪኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሰማረ መለሰ ጋር በአረንጓዴ ትራንስፖርት በተለይም የኤሌክትሪክ ተሽከራካሪዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ፈርመዋል፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አለሙ ስሜ ከምርምር ተቋማት ጋር መስራት ለተቋሙ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳለው ጠቅሰው ኢትዮጵያ የጀመረችውን የአረንጓዴ ትራንስፖርት እውን ለማድረግ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እና በቅርበት መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ባረኦ ሀሰን በበኩላቸው ዩኒቨርስቲዎቹ የተሽከርካሪ ስታንደርድ ከማውጣት ጀምሮ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በሰራቸው ስራዎች ላደረጉት ሙያዊ እገዛ ያመሠገኑ ሲሆን ስምምነቱ ስራዎችን ይበልጥ ለማስፋፋት አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ስምምነቱ የኤሌክትሪክ መኪኖች ጋር በተያያዘ ትግበራ፣መሠረተልማትን ማስፋፋት፣የመረጃ ስርዓቱን በጥናት እና ምርምር ማገዝ፣አመታዊ እና ወቅታዊ ሁነቶችን በጋራ ማዘጋጀት ፣የተሽከርካሪ ስታንዳርድ ትግበራ፣ የባትሪ አያያዝ እና አወጋገድ ፣ የሰው ሀበት ልማት እንዲሁም የማህበረሰብ ግንዛቤ መፍጠር ላይ ጥናት እና ምርምር በማድረግ ኢትዮጵያ በቀጠናው ያላትን መሪነት ይዛ እንድትቀጥል በጥናት እና ምርምር የተደገፈ ስራ በጋራ መስራት ያስችላል ብለዋል።
የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታ በበኩላቸው የአሁኑ ሰምምነቱ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ከዚህ በፊት ሲሰሩ የነበሩ ስራዎችን የበለጠ ሊጠናክር የሚያስችል ነው ያሉ ሲሆን ሀገር ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ዩኒቨርስቲው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የደብረ ብርሃን ዪኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሰማረ መለሰ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ዙሪያ ዪኒቨርስቲው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀው ስምምነቱም የበለጠ ትኩረት ሰጥተን እንድንሰራ ያስችላል ብለዋል፡፡
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃዎችን ለማግኘት