የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ
አስፈጻሚ መልዕክት
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በአስተዳደርና
ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሥር ከተዋቀሩ ሥራ አስፈጻሚዎች ውስጥ አንዱ የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ሲሆን
ባሳለፍነው 2017 በጀት ዓመት በፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች መዋቅራዊ አደረጃጀት ለውጥ መመሪያ ቁጥር 859/2014 መሠረት
የቋሚ ሠራተኞች ድልድል ተሰርቶ በአዲሱ አደረጃጀት መሠረት የሠራተኛ ስምሪት ተሰጥቷል፡፡ በምደባው በአመራር ደረጃ ወ 52 ሴ 16 ድ 68 በባለሙያና ሠራተኛ ደረጃ በድምሩ 734 ምደባ የተሰጣቸው ሲሆን በምደባው ሂደት ቅር የተሰኙ 64 ሠራተኞች ቅሬታቸው
በየደረጃው ባሉ አካላት እንዲታይ ተደርጎ 7 ትክክለኛ ቅሬታዎች ተመርምረው ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የሥራ ክፍሉ የዩኒቨርሲቲውን ዋነኛ
ተልእኮዎች ማለትም የመማር ማስተማር፤ የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በታቀደው ልክ ተፈጻሚ መሆን እንዲችሉ
የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡በመሆኑም በ2017 ዓ.ም በሁሉም ግቢዎች ያለው አጠቃላይ ሠራተኛ መምህራን 1425 ፣ አስተዳደር
ሠራተኞች 1372 ፣ቴክኒክ ረዳቶች 176 ናቸው፡፡
የሥራ ክፍሉ በሁለት ቡድኖች
ማለትም በሰው ሀብት አስተዳደር ፣ በሰው ሀብት ብቃትና ልማት ቡድኖች እና የሪከርድና ማህደር አገልግሎትን ጨምሮ የተደራጀ ሲሆን
የዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ እንዲሳካ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ
የሚገኝ ሲሆን ከተሰጡት ተግባራቶች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1.
በስትራቴጂያዊ ዕቅዱ ላይ የተቀመጡትን ዓላማዎች ለማሳካት የሰው ኃይል ፍላት
ዕቅድን አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ።
2.
የሰው ሀብት ሥራ አመራር ስምሪት ሥራዎች
በደንብ እና በመመሪያ መሠረት እንዲተገበሩ ማድረግ፤
3.
በዕቅድ እና በጥናት ላይ የተደገፈ
ስልጠና እንዲሰጥ ማስቻል እና የስልጠና ሂደቶችን መከታተልና መገምገም፤
4. የሠራተኞች
የሥራ አፈፃፀም ምዘና ከተቋም ዕቅድ አፈጻጸም ጋር የተናበበ
ሆኖ በወቅቱ እንዲሞላ ማድረግ፤
5. ሠራተኞች ግዴታቸውን እንዲወጡ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞቻቸውን እንዲያውቋቸውና
እንዲከበሩላቸው ማድረግ፤
6. ተጨማሪ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ
ማድረግ፤
7. የሠራተኞች የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት የተጠበቀ እንዲሆን መስራት፤
8. የሠራተኞችን ፋይል በአግባቡ አደራጅቶ መያዝ፤
9. የሠራተኞችን መረጃ በሥራ ክፍል፣በትምህርት ደረጃ፣በፆታ፣በዕድሜ፣በትምህርት
ዝግጅት በሀርድና በሶፍት ኮፒ አደራጅቶ መያዝ፤
10. በዕቅዱ መሠረት
እንዲሟሉ ለሚጠየቁ የሥራ መደቦች የሥምሪት ፍቃድ መጠየቅና በተሰጠው ፍቃድ መሠረት ማሟላት ፤
11. በሰው ሀብት አሠራር ዙሪያ ጥናቶችን ማካሄድ፤
12. ችግር ፈቺና ዘመናዊ የሰው ሀብት ሥራ አመራር እንዲመሰረት
መስራት፤
አባቢ ወርቅነህ ደስም
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ
አስፈጻሚ