የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ቤተ-መጻህፍት አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ ከተቋቋመበት 2014 ዓ.ም ጀምሮ በካምፓሱ ውስጥ ለሚያካሂዳቸው የመማር ማስተማር እና የጥናትና ምርምር ስራዎች ቁልፍ መሳሪያ ሆኖ ሲያገለግል የቆየ ተቋም ነው፡፡ በርካታ ምሁራን ትምህርትና ቤተ-መጻሕፍትን ነጣጥሎ ማየት እንደማይቻል በመግለፅ የቤተመጻሕፍት ሰራተኞችም እንደ መምህራን ሁሉ ተማሪዎች ለስልጠናቸውና ለጥናትና ምርምር ስራዎቻቸው የሚፈልጓቸውን መረጃዎች እንዲያገኙ በመጠቆምና በመምከር ከፍተኛ ተግባራት ማከናወን እንዳለባቸው በጥብቅ የሚያስገነዝቡት ነው፡፡ የቤተ-መጻሕፍቱም ዋና ዓላማ ዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን ተልዕኮ ማለትም ጥራቱን የጠበቀ ስልጠና፣ ጥናትና ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት በጥራት እንዲከውን የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተገቢ መረጃዎችና ማጣቀሻ መጻሕፍት በዲጂታልና በሃርድ ኮፒ በበቂ ሁኔታ እንዲያገኝ ማስቻል ነው፡፡ በዚህም መሰረት ቤተ-መጻህፍቱ ሶስት መሰረታዊ ተግባራት አሉት፡፡ እነሱም አንደኛ ስብስቡን በመጠንና በጥራት ማሣደግ፣ ሁለተኛ የተሰበሰቡትን መረጃዎች ተጠቃሚዎች በቀላሉና በፍጥነት ማግኘት እንዲችሉ በተገቢው ሁኔታ ማደራጀትና ሶስተኛ ለደንበኞች በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ የንባብ፤ የትውሰትና የምክር አገልግሎት መስጠት ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ተግባራት በጥራትና በፍጥነት ለደንበኞች ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ያለ የስራ ክፍል ነው፡፡
ወንደሰን በቀለ ሙላት Wondesen Bekele Mulat
Blenwondesen4 @gmail.com
0912741663