ማስታወቂያ

July 28, 2026

ማስታወቂያ


ቀን: 20/11/2018 ዓ.ም

በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በድህረ-ምረቃ (በመደበኛ እና በተከታታይ) ፕሮግራሞች ለመማር ለሚፈልጉ አመልካቾች በሙሉ።

በትምህርት ሚኒስቴር የሚዘጋጀው ሀገር አቀፍ የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ሐምሌ 29 እና 30/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የሚታወቅ ነው።

በመሆኑም ዩኒቨርሲቲያችን ለአመልካቾች ተገቢውን የዝግጅት ድጋፍ ለማድረግ እንዲያስችል በዩኒቨርሲቲው መምህራን የተዘጋጁ የማሰልጠኛ ማኑዋሎችን (Verbal Reasoning, Quantitative Reasoning, እና Analytical Reasoning) በይፋዊ ድህረ-ገጻችን ላይ የጫንን መሆኑን እንገልጻለን። አመልካቾች በዩኒቨርሲቲው ድህረ-ገጽ በመግባት ማኑዋሎቹን አውርዳችሁ እንድታነቡ እናሳስባለን።

በተጨማሪም ከሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በተመደባችሁበት አዳራሽ የማጠናከሪያ ትምህርት/ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው ሰዓት እንድትገኙ እናሳውቃለን።


ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ