Latest News

Latest News

ለድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ፣

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በተለያዩ የትምህርት መስኮች የ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ በመደበኛ (Regular) እና በተከታታይ (extension) ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በ2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተዘጋጅቶ የተሰጠውን የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መሠረት በማድረግ ዩኒቨርቲያችን 125 ጥያቄዎችን ከነመልሶቻቸው በማዘጋጀት ተፈታኞች እንዲዘጋጁበት ተደርጓል፡፡እነዚህን ጥያቄዎች በደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ Facebook ላይ ገብቶ ማየት ይቻላል፡፡ በመሆኑም ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲያችን ገብታችሁ ለመማር የምትፈልጉ ሁሉ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች በ2ኛና 3ኛ ዲግሪ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን አውቃችሁ የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተናውን Graduate Admission Test (GAT) በዩኒቨርሲቲያችን ለመፈተንና ለመማር እንድትመዘገቡ እያስታወቅን፣ ፈተናው በአ/አበባ ዩኒቨርሲቲ ተዘጋጅቶ በonline ላይ የሚሰጥ ይሆናል፡፡