ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ነሃሴ 14 /2017 ዓ.ም፡፡ ደብረ
ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሶስት የመጀመሪያ ዲግሪ የስርዓተ ትምህርት ፕሮግራሞችን በመሃልሜዳ ካምፓስ ለማስጀመር ወርክ ሾፕ አካሄደ፡፡
በእለቱ የመክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት የአካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ አለባቸው ጎሹሜ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል ለ3 የትምህርት ፕሮግራም መቀረጽ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን በመግለፅ ዩኒቨርሲቲው የተግባር ዩኒቨርሲቲ ከሆነበት ጀምሮ የትምህርት ክፍሉ መምህራን ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል ፡፡ አክለውም ለሚከፈቱት 3 ስርአተ ትምህርትፕሮግራሞችን ይዘን የቀረብን ሲሆን ለነዚህ ፕሮገራሞች ለረጅም አመታት በዘርፉ ሲሰሩ የነበሩ ሙህራን እንድተቹልንና እንድገመግሙልን በፕሮግራም ላይ ጋብዘናቸዋል በማለት ፕሮግራሙን ከፍተዋል፡፤
የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ዲን የሆኑት መ/ር ሙሃመድ
አህመድ እንዳሉት በመሃል ሜዳ ካምፓስ ለሚከፈቱ ለመጀመሪያ ድግሪ የሚሆኑ በባህሪያቸው ለየት ያሉ 3 ፕሮግራሞች (BA in
Finance, BA in Business Administration & Information System and BA in
Organizational Leadership & Project Management) ለሁለት ወራት ያህል ባለሙያዎች የዳሰሳ ጥናት ሲያካሄዱ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ቀጥለውም እነዚህ 3 ፕሮግራሞች በአካዳሚክ ግምገማ የተደረገባቸው መሆንን ተናግረዋል፡፤በተጨማሪም ከኢንዱስትሪዎችና ከሚመለከታቸው ተቋማት ግብአት ለማግኘት በፕሮግራሙ ላይ ተጋባዥ ሆነዋል በማለት ተናግረዋል፡፤
የመሃል ሜዳ ካምፓስ ዋና ስራ አስኪያጅ የሺአለም ጌታነህ (ዶ/ር) እንደገለፁት
በአዲሱ ካምፓስ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ ተግባር ተኮር የሆኑ ፕሮግራሞችን ከፍተን ለተማሪዎቻችን ምርጫ ለማቅረብ እንዲሁም ለኢንዱስትሪው ግብአት እንዲሆኑ በማሰብ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከሲቪል ሰርቪስ የመጡ ሙህራን 3ቱን ፕሮግራሞች በጥሩ ሁኔታ በመገምገማቸው እናመሰግናለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በመሃል ሜዳ በ2018 ዓ.ም በቢዝነስና
ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ስር ትምህርት ክፍል ለሚከፈቱት 3 ፕሮግራሞች ግምገማ ለማድረግ ከተለያዩ ኒቨርሲቲዎች ፣ከትምህርት ሚኒስቴር ፣ከሲቪል ሰርቪስ እና ከተለያዩ ባለድርሻአካላት የመጡ ሙህራን በቀረቡት ፕሮግራሞች ምልከታና ግምገማ ግብአት የጨመሩበት ፕሮግራም ነው በማለት የገለፁት የመሃል ሜዳ ካምፓስ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ዲን አቶ ዮሃንስ ተፈራ ናቸው፡፡
በእለቱም 3ቱም ፕሮግራሞች በመምህራን ቀርበው በባለሙያ ግምገማ ተደርጎባቸዋል፡፡
የመዝጊያ ንግግሩን ያደረጉት የሺ አለም ጌታነህ (ዶ/ር) እንደገለፁት 3ቱም ፕሮግራሞች በጥሩ ሁኔታ በመገምገማችው ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል፡፤