በደ/ብርሀን ዩኒቨርስቲ መ/ሜዳ ግቢ ለሚጀመሩ 3 ፕሮግራሞች የሰርዓተ-ት/ት (Curriculum) ግምገማ ተኪያሄደ

News news
2025-10-07 08:32:11

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ነሃሴ 14 /2017 .ም፡፡ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሶስት የመጀመሪያ ዲግሪ የስርዓተ ትምህርት ፕሮግራሞችን በመሃልሜዳ ካምፓስ ለማስጀመር ወርክ ሾፕ አካሄደ፡፡

በእለቱ የመክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት የአካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ አለባቸው ጎሹሜ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል 3 የትምህርት ፕሮግራም መቀረጽ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን በመግለፅ ዩኒቨርሲቲው የተግባር ዩኒቨርሲቲ ከሆነበት ጀምሮ የትምህርት ክፍሉ መምህራን ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል ፡፡ አክለውም ለሚከፈቱት 3 ስርአተ ትምህርትፕሮግራሞችን ይዘን የቀረብን ሲሆን ለነዚህ ፕሮገራሞች ለረጅም አመታት በዘርፉ ሲሰሩ የነበሩ ሙህራን እንድተቹልንና እንድገመግሙልን በፕሮግራም ላይ ጋብዘናቸዋል በማለት ፕሮግራሙን ከፍተዋል፡፤

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ዲን የሆኑት / ሙሃመድ አህመድ እንዳሉት በመሃል ሜዳ ካምፓስ ለሚከፈቱ ለመጀመሪያ ድግሪ የሚሆኑ በባህሪያቸው ለየት ያሉ 3 ፕሮግራሞች (BA in Finance, BA in Business Administration & Information System and BA in Organizational Leadership & Project Management) ለሁለት ወራት ያህል ባለሙያዎች የዳሰሳ ጥናት ሲያካሄዱ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ቀጥለውም እነዚህ 3 ፕሮግራሞች በአካዳሚክ ግምገማ የተደረገባቸው መሆንን ተናግረዋል፡፤በተጨማሪም ከኢንዱስትሪዎችና ከሚመለከታቸው ተቋማት ግብአት ለማግኘት በፕሮግራሙ ላይ ተጋባዥ ሆነዋል በማለት ተናግረዋል፡፤

የመሃል ሜዳ ካምፓስ ዋና ስራ አስኪያጅ የሺአለም ጌታነህ (/) እንደገለፁት በአዲሱ ካምፓስ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ ተግባር ተኮር የሆኑ ፕሮግራሞችን ከፍተን ለተማሪዎቻችን ምርጫ ለማቅረብ እንዲሁም ለኢንዱስትሪው ግብአት እንዲሆኑ በማሰብ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከሲቪል ሰርቪስ የመጡ ሙህራን 3ቱን ፕሮግራሞች በጥሩ ሁኔታ በመገምገማቸው እናመሰግናለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በመሃል ሜዳ 2018 . በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ስር ትምህርት ክፍል ለሚከፈቱት 3 ፕሮግራሞች ግምገማ ለማድረግ ከተለያዩ ኒቨርሲቲዎች ፣ከትምህርት ሚኒስቴር ፣ከሲቪል ሰርቪስ እና ከተለያዩ ባለድርሻአካላት የመጡ ሙህራን በቀረቡት ፕሮግራሞች ምልከታና ግምገማ ግብአት የጨመሩበት ፕሮግራም ነው በማለት የገለፁት የመሃል ሜዳ ካምፓስ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ዲን አቶ ዮሃንስ ተፈራ ናቸው፡፡

በእለቱም 3ቱም ፕሮግራሞች በመምህራን ቀርበው በባለሙያ ግምገማ ተደርጎባቸዋል፡፡

የመዝጊያ ንግግሩን ያደረጉት የሺ አለም ጌታነህ (/) እንደገለፁት 3ቱ ፕሮግራሞች በጥሩ ሁኔታ በመገምገማችው ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል፡፤

536267423_798891542469082_1016637676196489411_n-990286.jpg 536275447_798891499135753_6039070566808594316_n-532979.jpg 537713552_798891452469091_8462850940280489139_n-659348.jpg 536282540_798891419135761_6336357072665468445_n-509848.jpg 536271868_798891342469102_7489742208041623500_n-374408.jpg 537363306_798891259135777_8155901459255601424_n-265240.jpg 536267308_798891229135780_5178110298380744686_n-160268.jpg 536822357_798891199135783_8214848869158997005_n-699036.jpg