የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራሮች በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ጉብኝት አካሄዱ

News news
2026-08-18 11:14:44

ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም (አ/ወ/ጤ/ሳ/ካ) ። የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራሮች በዩኒቨርሲቲው የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ጉብኝት አካሄዱ።
በጉብኝቱ የኢፌዴሪ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር እና የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሰማረ መለስ፣ የቦርድ አባልና የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት፣ ሌሎች የቦርድ አባላት፣ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና የካምፓሱ ሥራ አስፈጻሚዎች ተገኝተዋል።
የቦርድ አመራሮቹ በጉብኝታቸው ወቅት የካምፓሱን ዘመናዊ የመማሪያ ክፍሎችና ላቦራቶሪዎች፣ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ፣ የተማሪዎች መኝታ ቤቶች እንዲሁም የግቢውን መሠረተ ልማትና የውበት ሥራዎች በመዘዋወር ተመልክተዋል።
በጉብኝቱም የካምፓሱ የመማርና ማስተማር ሁኔታ፣ የላቦራቶሪዎች አቅም፣ የተማሪዎች መኖሪያና መመገቢያ አገልግሎቶች እንዲሁም የግቢው መሠረተ ልማት አፈጻጸም በተመለከተ ምልከታ ተደርጓል።
ጉብኝቱ የካምፓሱን የሥራ አፈጻጸም በተጨባጭ ለማየት፣ ያሉትን ጥንካሬዎች ለማጠናከርና በቀጣይ የሚሻሻሉ ጉዳዮችን ለይቶ በመሥራት የተሻለ የትምህርትና የጤና ሳይንስ ሥልጠና አካባቢ ለመፍጠር ያለውን ትኩረት ያሳያል ።